Skip to main content

Posts

Our Featured Posts/ አዳዲስ እና ተነባቢ መጣጥፎች

ኤሳ ላሌ ፤ የቅድመ-ክርስትና የጋሞ–ወላይታው ነብይ (1880–1928)

ኤሳ ላሌ ፤ የቅድመ-ክርስትና  የጋሞ–ወላይታው ነብይ (1880–1928)ቅድመ ክርስትና አፍሪቃዊ እምነቶችን በተመለከተ ጥናት ሳደርግ ያገኘሁትን ኤሳ ላሌ የተባለ ነብይ ታሪክ በዚህ ፅሁፍ አስቃኛችኋለሁ። በተለይ ነጮች ወንጌልን ይዘውልን ከ ውጭ እስከመጡበት እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በጨለማ እንኖር እንደነበር አድርገው ለሚስሉ እና «የጨለማው አህጉር» (The Dark Continent) ብለው ለሚጠሩን ሁሉ የኤሳ ላሌ ታሪክ የሚነግረን ነገር አለ። ቅደመ ክርስትና የጋሞ–ወላይታ ባህላዊ አምልኮእንደ አብዛኛው የአፍሪካ ሕዝብ ሁሉ የኦሞቲክ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑት የ ጋሞ እና የወላይታ ህዝቦችም የራሳቸው ባህላዊ እምነት ነበራቸው/አላቸው።[1] ጋሞ እና ወላይታ በቋንቋ ፣ በባህል እንዲሁም በባህላዊ ሐይማኖታቸውም ስለሚመሳሰሉ ነው አንድ ላይ ለማየት የመረጥኩት።የጋሞ–ወላይታ (ኦሞቲክ) ባህላዊ ሐይማኖት የሁሉ ፈጣሪ በሆነ (Medhaga) ፣ የሁሉ የበላይ በሆነ በአንድ አምላክ (Saluwa Tossa) ያምናል።[2] «ሳሉዋ ጦሳ» ማለት የሰማይ አምላክ እንደማለት ነው። የጋሞ–ወላይታ ሕዝብ ክርስትናን ከመቀበሉ በፊት ይህንን አምላክ ያመልኩ ነበር። ሳሉዋ ጦሳ በጋሞ–ወላይታ ሕዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ነበረው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው «ጦሳ ጊኮ» (ጦሳ ከፈቀደ) ፣ ጦሳ እሬስ (ጦሳ ሁሉን ያውቃል) ወዘተ የሚሉ ንግግሮችን ማህበረሰቡ ውስጥ መገኘታቸው ነው።[3]በአምላክ (ሳሉዋ ጦሶ) እና በሰው መካከለኛ ሆነው በሚያገለግሉ «አያና» በሚባሉ መካከለኞች አሉ። እነዚህ «አያና» የተባሉ መካከለኞች የጦሶ ወካይ ሆነው በምድር ላይ ምስጋናን እና መስዋዕትን ይቀበላሉ። እንዲሁም ልመናን ወደ ጦሶ ያደርሳሉ ተብለው ይታመንባቸው ነበር።[4]የጋሞ–ወላይታ የባህል ሐይ…
Recent posts

ክርስቲያኖች እሬቻን እንዴት ማክበር አለባቸው? (ተግባራዊ ምክሮች)

ከሦስት ዓመት በፊት በፃፍኩት ፅሁፍ ላይ እሬቻን የሚያከብሩ ክርስቲያኖች ሊከተሏቸው የሚገቡ መንገዶችን ለመዳሰስ ሞክሬ ነበር (የፅሁፉን ሊንክ መጨረሻ ላይ አስቀምጫለሁ)። በተከታታይ ዓመታት ስለ እሬቻ እና ዋቄፈና ፅሁፎችን ፅፌያለሁ። ነገር ግን ስነመለኮታዊ ይዘት ላይ እንጂ ክርስቲያኖች ወደ እሬቻ እንዲሄዱ ከማበረታታት ውጭ ተግባራዊ እርምጃዎች ላይ ምክረ-ሃሳቤን አላስቀመጥኩም ነበር። በዚህኛው ፅሁፌ አጠር ያሉ ጠቃሚ ተግባራዊ ምክሮችን ለማስተላለፍ ሞክሬያለሁ። መልካም ንባብ።የአንድን ባህል ባዕላት አከባበር ክርስቲያናዊ ተግባራዊ እርምጃዎችን ማስቀመጥ ብዙ ነገር ማማከል ይጠበቅበታል። የመጀመሪያው ጉዳይ ሊታይ የሚገባው የበዓሉ ወይም የባህሉ ስነመለኮታዊ ይዘት ነው። እሬቻ በዓል ላይ የሚቀርበው ትችት አብዛኛው ስነመለኮታዊ ነው። እነዚህን ትችቶች ቀደም ባሉት ፅሁፎቼ ለመመለስ ሞክሬያለሁ። ስለዚህ ክርስቲያን እሬቻን በዓል ለማክበር ስነመለኮታዊ ኩነኔ (theological condemnation) እንደሌለበት እና የዋቄፈናው ዋቃ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ያሕዌ ጋር በባህርይ እና ገቢር ከመመሳሰሉም በላይ ያሕዌ ራሱን ለኦሮሞ ሕዝብ የገለጠበት ጥረታዊ እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ (Natural revelation) እንደሆነ ገልጫለሁ።ሁለተኛው ሊታሰብበት የሚገባው ነገር ቢኖር መንፈሳዊነት እና መንፈሳዊ ይዘት ነው። ይህ ማለት ክርስቲያኖች በዓል ሲያከብሩም መንፈሳውያን ናቸው። መንፈሳውያን ስንል በክርስቶስ ዳግም የተወለዱ (ዮሐ 3:6) የዋቃ ልጆች ናቸው (ዮሐ 1:12) ማለታችን ነው። ስለዚህ ምንም እንኳ እሬቻ ስነመለኮታዊ ሕፀፅ ባይኖረውም ሙሉ በሙሉ የተዋጀ ነው ማለት ግን አንችልም። ወይንም የአምላክ መንፈስ በዚያ የሚደረገውን ሁሉን ስርዓት ይቆጣጠራል ማለት አይቻልም። አይደለም…

የእሬቻን በዓል የማከብርባቸው 7 ምክንያቶች

[ይህ ጽሁፍ አጠቃላይ የእሬቻ በዓልን በተመለከተ ሲሆን የኮቪድ-19 ስርጭትን እና የጊዜውን ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ የ2013 እሬቻ በዓልን ማክበር የየግለሰቡ ኃላፊነት ነው።ከዚህ ባለፈ የግድ በቦታው (ሆራ ፊንፊኔ ወይም ሆራ አርሰዲ) ተገኝቶ ስለማክበር ይህ ፅሁፍ አይመለከትም።]በእሬቻ ዙርያ ክርስቲያኖች ሊኖራቸው ስለሚገባው አመለካከት ባለፉት ዓመታት ስፅፍ ቆይቻለሁ። በፅሁፎቼ የተማሩ ፣ አስተሳሰባቸውን የቀየሩ እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ደግሞ በሃሳቤ ያልተስማሙ በሰለጠነ መንገድ ሃሳቦቼን ለመተቸት እና ለመሞገት የሞከሩም ነበሩ። በቻልኩት መጠን ሁሉ ለአብዛኛዎቹ ጥያቄዎች መልስ ስሰጥ ቆይቻለሁ። በዚህ ዓመት ጽሁፌ ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት አልሞክርም። ይልቅስ እንድ አንድ ክርስቲያን የእሬቻን በዓልን ለምን እንደማከበር ምክንያቶቼን ዘርዝርያለሁ። በዚህም እግረ-መንገድ ብዙ ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረት አድርጌያለሁ። መልካም ንባብ።የእሬቻ በዓልን የማከብርባቸው 7 ምክንያቶች1) የእሬቻ በዓል ፈጣሪ (Umaa) ማመስገኛ በዓል ስለሆነእሬቻ ወይም እሬሳ ማለት የለመለመ አረንጓዴ ሳር ማለት ነው። ይህ በበዓሉ አከባበር ወቅት በእጅ የሚያዘውን ሳር ያመለክታል። ይህ ሳር ፈጣሪ (Umaa) በእሬቻ ቢራ ጊዜ ክረምቱን በሰላም ስላሳለፈ እና ባለፈው ዓመት ልምላሜን ስለሰጠ የማመስገኛ ምልክት ነው። በእሬቻ አርፋሳ ጊዜ ደግሞ መከር  ስለደረሰ እንዲሁም ጎተራን ስለሞላ ለፈጣሪ ምስጋና የሚደርስበት ጊዜ ነው።የሁሉ ፈጣሪ ፀሃይን ለቅዱሳን ለኃጥአን ሳይል የሚያወጣ አምላክ ሁሌም ምስጋና ይገባዋል። የእሬቻ በዓል ደግሞ ፈጣሪን ማመስገኛ ትልቅ ዕድል ነው።ለእስራኤላውያን የምስጋና የኢዮቤልዮ አመትን በየሰባት ዓመቱ እንዲያከብሩ እና ከመኸሩ በመውሰድ እንዲጠግቡ እና አምላካቸውን እንዲያመ…

“Jirra”, Hachalu Hundessa and the Christian Understanding of Existence

It has been 80 days since the famous Oromo singer and activist Hachalu (Oromo: Haacaalu) Hundessa was assassinated in still unclear to the public manner. Hachalu was a young charismatic and well experienced activist and singer. Although he had been identified with the popular movement of Oromo Protest of 2014–2017 that took the government to its knees, he was also a well singer of different issues beside struggle (Qabso). There have been different pieces of writings by influential figures on the life and legacy of Hachalu following his unexpected murder. Hence, my article will only focus on the philosophical and theological dimension of Hachalu's long known maxim, “Jirra” or “Jirtuu?”Some Background on “Jirra”It was in 2014 Hachalu released arguably his most loved single, “Maalan Jiraa” roughly translated as “Is this existence?” or “What existence of mine is this?” . The song was dedicated to the Oromo Protests that erupted following the Finfinne master plan proposed by the then g…